ዛሬም የደሀናና የጋዝጊብላ እናቶች የወላድነት አደራን ሊወጡት አልቻሉም። አባት የ13/14 አመቱን ጨቅላ ከማጨት በሕግ ቢከለከልም ያን ከማድረግ አላረፉም። ትምህርት ላይ መስፈንጠር የቻሉት ከእምዬ መሬት ቁጣ ቢላቀቁም ስለታቸው አሁንም የሚገባው ለደብረወይላ ቤተክርስትያን ነው። ለነሱ ላሊበላ የጦርነት መታሰብያ ወይንም የቱሪስት መዝናኛ፣ ለኛ ላሊበላ የታሪካችን ቅርፅና የውበታችን ማጌጫ፣ ለዛች ለጋ ወጣት ግን ጋሜናዋ ለተደፈነው ላሊበላ ድንጋይ ነው። ፀሎትዋን ታደርሳለች ለደብሬለዋ ማርያም። ቄሱም ሲያጉረመርሙ ትሰማለች፤ “አልተረፍንም ዘንድሮ፣ ምስጥ እኮ ቦረቦራት እመቤታችንን ወይ ማርያም። ” በሳይንስ የማይታይ በትምህርት የማይገለፅ የኛ ቄስ ሮሮ ለጋይቱ ጆሮ ውስጥ ሲንሳፈፍ ምን ይታያት ይሆን? ወጣትዋ። ብትጣበቅ ከድህነት መርጣ አይደል። ነፍስዋን ለፈጣሪ ትታ የመጣውን ሁሉ ችላ ትኖራለች። እናትዋ እንደሆነች በቃል አምና የሺ ሀረግ ብላ ሰይማታለች። እስዋም ተስፋዋ ይኸው ነው። “ወገብዋን ያበርታላት” ስትል የተማፀነችው ፈረንጅ አክስትዋ በመሀላቸው የሚገኘውን የኪሎሜትር ብዛት ቆጥራ አልጨረሰችም። የየሺ ሀረግን ታሪክ የላሊበላ ድንጋይ ይመሰክርላታል። በላሊበላ መስቀሎችም ስናጌጥ የየሺ ሀረግን ሕይወትና ተስፋ ትርጉም ለመስጠት እንጣር፣ በልባችን እንያዘው፣ አንድም ነፍስ ከንቱ አይደለችምና። አቤት ጊዜ ለእርስዋ እድገት ቢጨበጥ ከውልድ ተርፋ የሺ ማዕረግን ታሳድግና ላሊበላን ስናጌጥበት የፈጣሪ ብርሃን ኒኬሊን ወደ ወርቅ ይቀይርልናል። ሰምና ወርቁ ይግባቹህ። አንርሳ። የተኛ ዓያኑን ይግለጥ። #እኔም ዝም እንዳልል #የመስቀልዎ ልብወለድ
To this day, Dehana and Gazgibla mothers are unable to provide for their children. Fathers banned by law from marrying off their 13/14 year-olds haven’t stopped. Those who managed to escape from the wrath of Mother Earth are still making their vows to Debre Weila Mariam Church. For them, Lalibela is a war memorial or a tourist attraction; for us, Lalibela is the shape of our history and the essence of beauty, but for that young girl whose crown has covered over, Lalibela is not but stone. She delivers her prayers to Debre Weila Mariam. She hears the priest complaining, “They spare us not; this year, the termites are burying our Lady.” What does the young girl perceive from a lamenting priest? That escapes uncovering by education or science. A girl. Stuck, she didn’t choose poverty. She submits entirely to the Creator and takes everything as it comes. Her mother named her carefully – Yeshihareg, a thousand vines. Her name is her only hope. Her alien aunt, who has not finished counting the miles between them, pleads, “May God strengthen her back.” Lalibela’s rocks testify to Yeshihareg’s story. As we adorn ourselves with the Lalibela cross, let us strive to give meaning to the life and hope of Yeshihareg, to hold her in our hearts, for not a single life is in vain. If time can save her, she will birth Yeshimaereg, a thousand ranks, as we adorn in the Lalibela jewels, for the light of the Creator will turn tin into gold. Dare to separate the wax from the gold. Let’s not forget. Open all sleeping eyes. # I’m not going to keep quiet #the storyteller from Meskelo