የወለዳትፈረደባት

ይነገር፣ ይወራ፣ ይሰማ፤አባት ልጁን ፈጀ።ምን ቢፈረድ፣ ምን ቢቀጣ፣የጨመደደው ሕይወት አይፈታ።እሷ እናት ሆና ታማችእሱ አባትዋ ደፍሯት። ይታሰብ ድንጋጤዋ፣ብርክርክ ነፍስዋ፤በአሥርና አራት ዓመትበሽብር ተጠምቃየዘጠኝ ወር ሸክምየእድሜ ልክ እስራት ተቀብላ። የወለዳት እንደፈረደባትይፈርዳል ታዛቢም፤ሰቆቃዋ አይወለድ፣እየተገላበጠ ያራል እንጂ።ትሁት ማርያም ድረሽላትልጇም ይደግ እንግዲህ። ይናገር ግን የታሪክ አዋቂ፣ያሰረዳ የጤና መርማሪ፤ልጅን የሚያስመኝ ልክፍትነቀርሳው እንዴት ይገፈፍ?ይጠብቅ ጎሮቤት የሰፈሩን ሕፃን፣ይታሰር ይመርመር ይጥፋ የዚህ ልክፍት ሰይጣን።

ትርምስ / Chaos

https://youtu.be/mYpxRTCvhkM ትርምስ በአንዳንድ ሰዎች እይታ አስማት፣ ወይንም የሂሳብ ፅንሰ-ሀሳብ፣ አልያም ላልተራቀቀው በደፈናው የሕይወት እውነታ ነው። እዚህ የትርምስን አተረጓጎም የምንቃኘው በቃሉ መሰረት ትርምስን በመፍጠር ነው። አቅራርቡ ለዘብ ባለ መልኩ ትርምስን ይወክላል፣ ማለትም ሰዎች በእለት ኑሮ ገጠመኞቻቸው ትርምስን በሚቃኙበት -  በትራፊክና  በዜና ጫጫታ፣ በገበያ ሩጫ፣ በመሥሪያ ቤትም በመኖርያ ቤትም ባለው የስራና ሓላፊነት መብዛት ወዘተ።  ምንም የከፋ ነገር … Continue reading ትርምስ / Chaos