ይነገር፣ ይወራ፣ ይሰማ፤
አባት ልጁን ፈጀ።
ምን ቢፈረድ፣ ምን ቢቀጣ፣
የጨመደደው ሕይወት አይፈታ።
እሷ እናት ሆና ታማች
እሱ አባትዋ ደፍሯት።
ይታሰብ ድንጋጤዋ፣
ብርክርክ ነፍስዋ፤
በአሥርና አራት ዓመት
በሽብር ተጠምቃ
የዘጠኝ ወር ሸክም
የእድሜ ልክ እስራት ተቀብላ።
የወለዳት እንደፈረደባት
ይፈርዳል ታዛቢም፤
ሰቆቃዋ አይወለድ፣
እየተገላበጠ ያራል እንጂ።
ትሁት ማርያም ድረሽላት
ልጇም ይደግ እንግዲህ።
ይናገር ግን የታሪክ አዋቂ፣
ያሰረዳ የጤና መርማሪ፤
ልጅን የሚያስመኝ ልክፍት
ነቀርሳው እንዴት ይገፈፍ?
ይጠብቅ ጎሮቤት የሰፈሩን ሕፃን፣
ይታሰር ይመርመር ይጥፋ የዚህ ልክፍት ሰይጣን።