አዳኙ ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚያስታወስ አጭር ተርት

2013 ዓ.ም. ፣ ላንደን ከተማ

ከግል ማሕድር፣ ያልተመዘገበ ሰዓሊ

አንድ የእጅ ሙያተኛ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት የወለት ጊዮርጊስን ብዋንባ ለመስራት ወደ መኖርያ ቤትዋ ሂደ። ከመግቢያ በርዋ ፊትለፊት በሚገኘው ግድግዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተግዋታቹን አውሬ በጦር ወግቶ ሲያጠፋ የሚያሳይ ምስል ተሰቅሎ በማግኘቱ ቆም በሎ ተመለከተው።

“በእንጨት መደብ ላይ የሰፈሩት ቀለማት ከተፈጥሮ የመነጩ ናቸው” ብላ አስረዳችው ወለተ ግዮርጊስ። 

ፈረንጁ ቧንቧ ሰራተኛ ትክ ብሎ አያትና መልስ ሳይሰጣት ወደ ስራው ሄደ። እርስዋም ምኞትዋ የመጣበትን ስራ ቶሎ አገባዶ እንዲሄድ ነብርና ስራውን አብቅቶ ወደ መውጫው በር ሲያመራ በዓይኗ ተከተለችው።  ቤትዋን ለቆ ከመሄዱ በፊት አንድ አፍታ እንደገና ቆም ብሎ በአይኑ እንደገና የጊዮርጊስን ስዕል ቃኘ፡፡

በስዕሉ መማረኩን አይታ “ፎቶ ማንሳት ከፈለክ አንሳው” ብላ ወለተ ፈቀደችለት።  አሁንም ትክ በሎ አያትና ፎቶግራፉን ካነሳ በኋላ “አመሰገናለሁ” ብሏት መንገዱን ቀጠለ።

 “ሰማህ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ለሰውየው ክርስትና አባቴ እንደሆንክ ብነግረውማ ኖሮ ምን ሊል ኖርዋል” ብላ ወለተ ጊዮርጊስ በሆድዋ ሳቅ አለች ። በልጅነት እድሜዋ ባልንጀሮችዋ ከክርስትና አባትና እናቶቻቸው ሰጦታ ሲቀበሉና ግብዣ ሲጋበዙ አይታ “ምን አል ለኔም ሰው የሆነ የክርስትና አባት ቢኖረኝ ኖሮ” ብላ ማሰብዋን አስታወሰችህ። ብሶትዋነም ያዳመጠ “ሰውን ከማመን ቅዱሳንን ማመን ይሻላል፤ ለመሆኑ የትኛው ታማኝ ጓገደኛ ኖሮ ነው ልጅ በአደራ የሚሰጥው?” ብለው ምላሽ የሰጥዋትንም ሰዎች አስታወሰች።  ወላጆቿ ግን ስለ ጉዳዩ ያጫወትዋት ታሪክ ለየት ያለ ነበር።

1951 ዓ.ም. ፣ ሃረር ከተማ

በአንድ ውቅት በተወዳጅነት ይታወስ የነበረ መዝናኛ  

በወቅቱ የሃረር ወጣቶች የሚጠበቅባቸውን ጉብዝና በዓለም ለማሳመስከር ጉጉተኛና ደሰተኛ ነበሩ። ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ በትምህርታቸውና በአመላቸው የተመሰገኑትን ወጣት የጦር ካዴት ግብረሃይል በከፈቱት የሃረር ጦር ሃይል ማሰልጠኛ መአከል መመደባቸወን አሳወቁ።

ለሰልጣኞቹ የተዘጋጀው ማርፍያ ቤት ካጌጠውና ዝና ካተረፈው ዘመናዊው ራስ ሆቴል እምብዛም አይርቅም ነበር። የማሰልጠኛው መአከል አሰልጣኞችና ባለሰልጣኖችንም ለማስተናገድ ዝግጁ የሆነ በረንዳ፣ የመጠጥ ባንኮኒ፤ የምግብ እንዲሁም የመዝናኛ አዳራሽ ኑልኝ ኑልኝ በሚል ግብዣዊ ስሜት ምኞቱን ያስተጋባ ነበር።  

ከሆቴሉም ወደ ምስራቅ አለፍ ብላ፣ በ82 መስጊዶችና በ368 ጠመዝማዛ መንገዶች የታጀበች፣ በጥንት ታርክዋ ብርካታ ሱልጣኖችን ያስተናገደች፣  በዓለም የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በአራተኛ ደረጃ የታወቀችው ቅዱስ ከትማ፣ እንዲሁም ዛሬ በየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአለም ቅርስ ሆና የተመዘገበችው የሃረር ከተማ እምብርት ጀጎል ናት።

በጀጎል ግንብ ተመሽጋ በሃረር ከተማ የምትገኘው ጥንታዊ ማእከል በጠባብ መንገዶችዋ ላይ ሞቅ ያለ የንግድ እንቅሰቃሴ ታስተናገድ ነበር።  እንደ ፅሐይና ንግስቲ የመሳሰሉ ወጣቶችም ለልብስ ሰፊአቸው ልካቸውን ለመስጠት ሽርጉዱ መሃከል ይንቀሳቀሳሉ። በወጣቶች ዘንድ ተውዳጀነት ያተረፉትም በርካታ ጌጥ፤ ጌጣጌጦች፣ ልዩ የፅጉር አሰራርና የሽቶ ዓይነቶችም በገበያው ይገኙ ነበር።

ከጀጎል ግንብ አለፍ ብሎ የሚገኘው የምግብ መሸጫ ገበያ ለክርስትያንና ለእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በሁለት ጎን ተመቻችቶ ተገቢውን የምግብ ሽያጭ ያከናውን ነበር። የጦር ማሰልጠኛው እጩ መኮንኖችና አሰልጣኞቻቸውም ሳምንታዊ የምግብ ቀለባቸውን ለመሸመት በቦታው ይገኙ ነበር። በመሃላቸውም ፅጉራቸውን አሳምረው፣ በአዲስ ልብስና ጌጣጌጥ ተውበው፣ እንደ ጽጌረዳ ያማረ መአዛን አዝለው የሚያልፉት ውብ ውጣት ልጃገረዶች አፋቸወን በመገረም አስከፈተው ያስቀርዋቸው ነበር።

ከዊኪፒድያ ድሕረ ገፅ

ፅሐይና ንግስቲ ትኩስ የተስራ ፅጉራቸወን በነጠላ ሸፈን እያደረጉ በገበያው መሃል ሲንሸራሸሩ እጩ መኮንኑ በካኪ ቀለም ጨርቅ እንደ እግረ ጠባብ አጠር ያለ ቦላሌ መሳይ ሱሪ ታጥቀው ከላይ ደግሞ በደረት ቁልፍ ኮሌታቸውን ወደታች ሳብ አድርጎ እንዲይዝ ተደርጎ የተሰፋላቸወን የደንብ ልብስ አሸብርቀው ላይ ታች ሲሉ በቆረጣ ሾፍ ሾፍ መደራረጋቸው አልቀረም። በቦታው የነበሩትም ህዝባዊ ጎሮምሶች በኮረዳዎቹ በመማርክ “እኛንም እዩን እንጂ” ለማለት ይመስል ፉጨትና ልዩ ድምፃ ድምፅ ብያሰሙም ልጃገርዶቹ እንዳልሰማ ሆነው ያልፏቸዋል። ከጎርምሶቹም መሃካል የዌራ ቅብ ቆዳ ያላትን ፅሀይን አይቶ ልቡ የደነገጠው ጣልያኑ ዊልያም ነበር።

ከብዙ ወራት ደጅ ጠናት በኋላ ፀሐይ ባቀረበችለት የሰላምታ ምልክት ከመጽናንትም አልፎ በንግግር ሊያግባባት የተዳፈረው ዊልያም ከፀሐይ ጋር መግባባት ጀመረ። የቅዱስ ጊዮርጊስ የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ተከታይ ስለመሆንዋም ተረዳ። በበኩሉ የምስራቃዊ እምነት ተከታይ እንደሆነ ሲነግራት ቀፈፍ እንደማለት ሲላት ታወቀው። ለወዳጆቹም ይህንኑ ሲነግራቸው እንዲታገስ መከሩት።

ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ዊልያም ድንገት ታመመ። ያጋጠመው ትኩሳት የእግር መገጣጠምያዎቹን አሳብጦ ቀንና ሌሊት አወራጨው። ይህንንም ልብ ያሉ ጎሮቤቶቹ ካፌኖልና አስፕሪን፣ የጤናዳምና የጦስኝ ሻይ ከፍትፍት ጋር ቢያቀርቡለትም ህመሙ እየናረ እንጂ እየተሻለው አልሄደም። ፍቅር ለበሽታ ያጋልጣል ብለውም ስላመኑ ፅሐይን አስፈለገው አስጠሯት።   ፅሐይ በቦታው ተገኝታ ዊልያምን ታሞ ሲማቅቅ በማየትዋ ደንገጣ ፈረጠጠች። ድንገትም በላስቲክ የተጠቀለሉ ጠርሙዞች ይዛ መልሳ ከተፍ አለች።

“የግዮርጊስ ጠበል ነው” ብላም በእይታ ሲገመግምዋት ለነበሩት ጎሮበቶቹ ነገረቻቸው። እንሱም ጠበሉን በብርጭቆ ሞልታ ዊልያምን በክንድዋ ደገፍ አደርጋ ስታጠጣው ተመለከትዋት። ከዛም ያበጡትን እግሮቹን በፅበሉ እጥብ አድርጋ በጋቢ ጠቀለለቻቸውና ሻማ አብርታለት ሄደች። ዊልያም ሙሉ ቀንና ሌሊት በሰላም ተኝቶ ዓይኑን ሲገልጥ ድካም ቢሰማውም የተንገላታበት ህመም ሙልጭ ብሎ ጠፋለት። የእህል ውሃ ፈላጎቱ በመመልሱ ጎሮቤቶቹ እፎይ በለው ለቤተክርስቲያን ምስጋና ማቅረብ እንዳለበት ተመካክርው ተሰብሰበው ይዘውት ሃዱ።

ከዊኪፒድያ ድሕረ ገፅ

ቤተክርስቲያን ደርሰው ጫማቸውን አውልቅው ከወለሉ ላይ እየተቀመጡ ሳለ ቄሳወስቱ ከወደ መቅደስ ውስጥ ሆነው የቅዱስ ያሬድን መዝሙር ይዘምሩ ጀመር። ቤተክርስትያኑ በእጣን ታወዶ ነበር እና ልብ ብሎ ያያቸውም አልነበረም። ከበሮው፣ ጽናጽሉ እንዲሁም በካህናቱ ድምፅ የታጀበው የምስጋና ሥራዓት በውስጣቸው ተዋህዶ እንደመፍዘዝ እስኪሉ አስተጋባባቸው።

ዋይ ዜማ ዘሰማዕኩ በሰማይ

እመላዐክት ቅዱሳን እንዘ ይብሉ

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ

እግዝያብሔር መላህ ሰማያት ወምድር

ቅድሳት ስብሃ ቲከ

በሰማያት የሰማሁት የመላእክት ዜማ

ምን ያምር ምን ያምር

የሰማሁት የመላእክት ዜማ

ምን ያምር ምን ያምር

የሰማሁት የመላእክት ዜማ . . .

ሲል ይቀጥላል መዝሙሩ – ሙሉውን ለማዳመጥ በመምህር መንክር ሃዲስ የተዘጋጀ ይህን ድህረ ገጽ ይጎብኙ፡

https://www.youtube.com/watch?v=1IfCaBl5lw0

ቅዱስ ጊዮርጊስ ለኢትዮጵያም ሆነ ለእንግሊዝ፣ ለሌሎችም በርካታ ሃገሮች ጨምሮ የበላይ ጠባቂ ነው ተበሎ ይታመናል። ለወለተ ጊዮርጊስ ብቻ ሳይሆን በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ህጻናት ደግሞ የክርስትና አባት ከመሆኑም አልፎ ዘመን ተከትሎ ለቁጥር የሚታክቱ የንግድ ድርጅት ምልክት እና ከደቡብ ምሰሶ እስከ ሰሜናዊ ምሰሶ ድረስ ያሉ በርካታ ምልክቶችን እና መድረሻዎችን ያስመዘገበ ጂኦግራፊያዊ መለያ ነው።

Your comments are always useful, I'd love to hear from you.