ለሴቶች ክብር

ለእህቴ

ለአንቺ ለውዲቱ
እንጨትና ቅጠል ለተሸከምሺቱ
አይዞሽ እናት አለም
ቀን ያልፋል ግድ የለም
አትድፊ አንገትሽን
ይሉቁን አብስሪ ሃያል መሆንሽን
በተሸከምሽው ስር ሃያል ተስፋ እንዳዘልሽ
ከቅጠሎቹ ስር ብርሃን እንደታየሽ
እህቴ አትርሺ
ነገ ሌላ ቀን ነው ታሸንፊዋለሽ

ለእቴ ላንቺ ለዶክተርዋ
በርችልን አንችዋ
መድሃኒት ነው እጂሽ
ተስፋ ነው ፈገግታሽ
አበርቺ ነው ምክርሽ
እናማ እህት አለም
ለአንቺ የገባሽ ለነሱ ያልታያቸው
ያንቺ ህልም ለነሱ ቅዠት ሆኖባቸው
እንቅፋት ሊሆኑሽ
መንገድ ሊዘጉብሽ
ቢከጂል ልባቸው
ተይው እናት አለም ጨርሶ አትስሚያቸው
የውስጥሽን መብራት እንዳታጨልሚ
ሁል ግዜ ለምልሚ

ለእህቴ ላንቺ ለመምህርዋ
እውቀት አካፋይዋ ለአምሮ አናጭዋ
ለነገ ተተኪ ትውልድ ገንቢ ነሽ
እውነትን ያለ ውስጥሽ
በርችልን እቴዋ እንዳትቆርጭ ተስፋ
ለእውነት የቆምሽበት ብርሃንሽ አይጥፋ።

ለቤት እመቤቷ ለቀንቺ ለእህቴ
ታላቅ ነው ክብረቴ
እናትነት መርጠሽ
ለልጆቼ ብለሽ
ለዋልሽው ከቤትሽ
የአነጽሻቸው ልጆች ምስጋና ይድረስሽ
ይታይ ብርሃንሽ።

ለእህቴ በባእድ አገር ላለሽ
የስራ ክብደቱ
የሰዉም ክፋቱ
ምንም ሳያግርሽ
ለወገን ለደረስሽ
እህትሽን ላስተማርሽ
ወንድምሽን ላቋቋምሽ
ለወንችም ለውዲቷ ምስጋና ይድረስሽ።

ለእህቶቼ ሁሉ
በአለም ዙሪያ ላላችሁ
እንኳን ለሴቶች ቀን በሰላም
ደረሳችሁ።

እንደወረደ የሚባል ግጥም
15 ደቂቃ ቀኑን ለማክበር

ተጻፈ

©እመቤት መንግስቴ

©Emebet Mengiste, 8 March 2021, Atlanta

Your comments are always useful, I'd love to hear from you.